• Post category:News
  • Post comments:0 Comments

ለህዝብ መስራት ያሸልማል! ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ለመሀበረሰብ አገልግሎት!

የሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት እና የሐራምቤ ቢዝነስ ግሩብ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፈይሳ አራርሳ ከ12 ሚሊየን ብር በላይ በማውጣት በአዳማ ከተማ ላሰሯቸው የመሀበረሰብ አገልግሎት የበጎ አድራጎት ስራዎች የአዳማ ከተማ መስተዳድር 1ኛ ተሸላሚ ሆነዋል!
የአዳማ ከተማ መስተዳድር በህዝብ ተሳትፎ የሚሰራቸውን የመሠረተ ልማት ስራዎች በመደገፍ የሚታወቁት የሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት እና የሐራምቤ ቢዝነስ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፈይሳ አራርሳ በሀገሪቱ ውስጥ ከሚሰሯቸው ትልልቅ የኢንቨስትመንት ስራዎች ጎን ለጎን በበጎ አድራጎት ስራውም ከፍተኛ መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ የሚታወቁ ሲሆን በአዳማ ከተማም ከ12 ሚሊየን ብር በላይ በማውጣት ትምህርት ቤቶችን እንደዚሁም የከተማዋን የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ያሰሩ ሲሆን ለዚህም ውለታቸው የአዳማ ከተማ መስተዳድር ከተማዋ አንደ ኦሮሚያ አንደኛ በመውጣት ፕሬዚደንሽያል አዋርድ በማግኘቷ ምክንያት እና ለዚህም ትልቅ አስተጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች እና ተቋማትን ለማመስገን በተዘጋጀው ፕሮግም ላይ አቶ ፈይሳ አራርሳ ከ12 ሚሊየን ብር በላይ በማውጣት ለሰሯቸው የበጎ አድራጎት ስራዎች እና ላበረከቱት እጅግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የከተማ መስተዳድሩ በአንደኝነት ደረጃ የክብር ሽልማት ከታላቅ ምስጋና ጋር አበርክቶላቸዋል።
ነሀሴ 14, 2014ዓ.ም
አዳማ

Leave a Reply